null The House in its 47th regular session approved the appointment of Ethiopian Human Rights Commission (EC).

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 47ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዕጩ ኮሚሽነር ሹመትን መርምሮ አፀደቀ፡፡

ምክር ቤቱ ሰኔ 25 ቀን 2011 ባካሄደው 47ኛ መደበኛ ስብሰባው 9 የሚሆኑ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መክሯል፡፡

ም/ቤቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዕጩ ተቯሚ ኮሚሽነርን አስመልክቶ በቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ተወያይቶበታል፡፡ የምልመላው ሂደት ሰባት መስፈርትን መሰረት ያደረገ እና ዜጎች ግንዛቤ እንዲኖራቸው በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ በመስጠት 73 ወንዶችና 15 ሴቶች ባጠቃላይ 88 ግለሰቦች ለምርጫ እዲጠቆሙና እንዲሳተፉ መደረጉን በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

ም/ቤቱም ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ሙሉጌታን ኮሚሽነር አድርጎ በአንድ ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል፡፡

የም/ቤት አባላት በበኩላቸው አዲሱ ኮሚሽነር ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸው ሳይሸራረፍ ስራ ላይ እንዲውል በማድረግና ያላቸውን የስራ ልምዳቸውን ከመጠቀም በተጨማሪ በአዋጁ አንቀጽ 6 ላይ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በብቃትና በታማኝነት የመምራት ሚናቸው ይወጣሉ ሲሉ ስራው ትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ በሙሉ አቅማቸው መስራት እንዳለባውም አንስተዋል፡፡

በማስከተልም ም/ቤቱ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ የተወያየ ሲሆን፤ የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ን/ሰብሳቢ የሆኑ ወ/ሮ የሺእመቤት ነጋሽ የውሳኔ ሃሳብ ለም/ቤቱ ባቀረቡት ወቅት ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ለማቋቋም የቀረበውን ይህ ረቂቅ ደንብ በዋናነት ድርጅቱ ለማህበረሰቡ ጊዜውን የጠበቀና ታማኝ መረጃ በማድረስ፣ በማስተማርና በማዝናናት እና የዜጎችን ሃሳብ የመግለጽ ህገ መንግስታዊ መብትን ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም የተለያዩ አመለካከቶችንና አስተያየቶችን በማስተናገድ በህዝቦች እኩልነት እና መፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ላይ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ረቂቅ ደንቡም ድርጅቱ በክልሎችና በማናቸውም ስፍራ ቅርንጫፍና ወኪል ሊኖረው እንደሚችልም ይደነግጋል፡፡ በተጨማሪም ዜና አገልግሎት ድርጅቱ ከመንግስት ከሚመደብለት በጀት ባሻገር ዜና፣ ዜና ነክ ዘገባዎችና ፕሮግራሞችን በመሸጥት የራሱ ገቢ ሊያመነጭ ከመቻሉም በተጨማሪ በአዋጁ በተሰጠው መሰረት የህዝብና የንግድ ማስታዎቂያዎችን በመስራትም ገቢውን ማሳደግ እንደሚችልም ነው ደንቡ የሚያስቀምጠው፡፡

 

ም/ቤቱም በአገሪቱ የሚገኙ ባህሎችን፣ ወጎችን፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን ለአገር ውስጥና ለውጭ አለማት በማስተዋወቅ ብሎም ገጽታን በመገንባት አያሌ ድርሻ ያለውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ ደንቡ ተቀብሎ በአንድ ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡

በመጨረሻም ም/ቤቱ አሁን ላይ በዘፈቀደ የሚከፈቱ የትምህርት ፕሮግራሞች መበራከት በትምህርት ጥራት ላይ የሚያስከትለውን ችግር ለመግታት እና የትምህርት ፖሊሲ እድገታችን ከደረሰበት ደረጃ ጋር ተጣጥሞ እንዲሄድ የሚያስችል በእውቀት ብቁ የሆነውን የሰው ሀይል ለማልማት ድርሻ የጎላ የሆነውን የከፍተኛ ትምህርት ረቂቅ አዋጅ ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በሁለት ድምጸ ታቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል፡፡