null The House said road projects need follow ups and support to finish on due time and budget.

የመንገድ ፕሮጀክቶችን ማስጀመር ብቻ ሳይሆን በቂ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ  በተቀመጠላቸው ጊዜና በጀት እንዲጠናቀቁ  መሰራት እንዳለበት ምክር ቤቱ ገለፀ፡፡

ምክር ቤቱ ይህን የገለፀው ሚያዚያ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአካሄደው 35ኛ መደበኛ ስብሰባው የትራንስፖርት ሚኒስቴርን የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በገመገመበት ወቅት ነው፡፡

ሚ/ር መ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ስራዎች የበለጠ አቅም እዲኖራቸው በአምስት ንዑስ ዘርፍ በመለየት ማለትም በመንገድ፣ በባቡር ልማት፣ በማሪታይምና ሎጂስቲክ አገልግሎት እና በአቪዬሽን ዘርፍ በመከፋፈል ለአብነትም በመንገድ ስራ ዋናና አገናኝ መንገዶችን ደረጃ መሻሻል እንዲሁም ወቅታዊ ጥገና በማድረግ ህብረተሰቡን በዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ የትራንስፖረት ሚንትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ አዳዲስ የመንገድ ግንባታ ማከናወን ብቻም ሳይሆን የተገነቡትን ደህንነታቸውን ለማስጠበቅም ተጨማሪ የመንግድ ጥገናና ግንባታ ለማድረግ የሚያስችል የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ  መታቀዱም  ተገልጿል፡፡

ከአባላት፣ ከቋሚ ኮሚቴና ከህዝብ ለተነሱ ጥያቄዎች በሚ/ር መ/ቤት አመራር አባላት ምላሽ የተሰጠ ሲሆን አገሪቱ በርካታ የመንገድ መሰረተ ልማት ፍላጎት ያላት ቢሆንም በበጀት ዓመቱ 299 የሚሆኑትን ፕሮጀክቶችን የማስጀመር ስራ መሰራቱ ተብራርቷል፡፡

የበርካታ መንገዶች ፕሮጀክት ስራ የሚጀመር ቢሆንም ሳይጠናቀቁ መጓተታቸው ይስተዋላል የሚል ጥያቄ ምክር ቤቱ ያነሳ ሲሆን፤  ከወሰን ማስከበር ጋር ተያያዞ የሚያጋጥሙ ችግሮች ፣ የኮንትራክተሮች የአቅም ውስንነት እና የበጀት እጥረት መኖር  ዋና  ዋና ማነቆዎች መሆናቸው ተገልጿል፤ እየተሰሩ ያሉ መንገዶች ከፍተኛ የጥራት ችግር እንዳለባቸው ዘርፉን የሚከታተለው የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽንና ትራስንፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴው  ባአካሄዳቸው የመስክ ምልከታዎች መገንዘብ የተቻለ ሲሆን፤ዋነኛ ምንስኤውም  የግብዓት ዕቃዎች ጥራት መጓደል  መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተሸከርካሪዎች ፍላጎት ማጣት፣ መጋዘኖች መሙላት፣ ለማራገፍ ቦታው ምቹ አለመሆንና የጫኚ አውራጆች በክፍያ አለመስማማትየጭነት ትራንስፖርት ስምሪት አገልግሎት ዘርፉን  ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት እየተገዳደሩት ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የመንገድ ትራንስፖርት ስምሪት ለማሳደግ ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በፌዴራል ትራንስፖርት ስር በሚተዳደሩ አምስት መናኻሪያዎች እድሳት በማድረግ የክትትልና ድጋፍ ስራ የሚታየውን ወከባና ግርግር ለማስቀረት ቢሰራም በመርካቶ መናኻሪያ ላይ ማስተካከያ እርምጃዎች ቢወሰዱም  በተለይ በዓላት ሲደረሱ  በርካታ ቅሬታ ማስነሳቱ እንደቀጠለ  ሲሆን፤  በትራንስፖርት ስምሪት ዘርፍ ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት በቀጣይ የተጠናከረ ስራ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እንደሚሰራ አስታውቋል፡፡

የትራፊክ አደጋን በተመለከተም የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ በርካታ መኪኖች አገር ውስጥ እየገቡ ለትራፊክ አደጋ፣ ለአላስፈላጊ ነዳጅ ፍጆታ እየዳረጉ እና ለትራስፖርት እንቅስቃሴውም እንቅፋት እየሆኑ በመሆናቸው ለችግሩ መፍትሄ ለማበጀት ሚ/ር መ/ቤቱ ከገቢዎችና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየመከረ ይገኛል፡፡ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ የሚገኙ ሲኖ ትራክ መኪኖች ላይም የፍጥነት መገደቢያ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

 የተነሱ ጉዳዮችን በግብዓትነት  በመውሰድ ሁሉን አቀፍ የመንገድ ተደራሽነት እና  ፍትኃዊነት በአገሪቱ  ለማረጋገጥ እንዲቻል ሚ/ር መ/ቤቱ በትኩረት እንዲሰራ   ም/ቤቱ አሳስቧል፡፡