null The Small Finance Amendment Proclamation helps Ethiopians abroad to become active in economic and social sectors.

የአነስተኛ ፋይናንስ ማሻሻያ አዋጁ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያግዛል ተባለ፡፡

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5 ዓመት የስራ ዘመን አንደኛ መደበኛ ስብሰባ የመድን እና የአነስተኛ ፋይናንስ ስራዎችን ለማሻሻል የቀረቡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ለገቢዎችና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መርቷል፡፡

የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ አንባስደር መስፍን ቸርነት እንደገለጹት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በፋይናንስ ዘርፉ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ አገሪቱ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ከምታደርገው ድርድር እንደማይጋጭ እና የአክሲዮን ግዥው የሚካሄደው በኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን ባላክሲዮኖቹ የሚያገኙት የትርፍ ድርሻ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባላክሲዮን እንደሚከፈላቸው አስረድተዋል፡፡

ኪዚህ በፊት በነበረው አዋጅ ለአሰራር እንቅፋት የሆኑ አንቀፆች እንደነበሩበት የገለጹት አንሳደር መስፍን ማሻሻያ አዋጁ በዋናነት የአነስተኛ ፋይናንስ ተቋማትን አላማ፣ የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ጥበቃ በተመለከተ እና ከወለድ ነጻ አገልግሎት አስጣጥ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተመሳሳይም አንባሳደር መስፍን የመድን ስራ አዋጁ መሻሻል ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ውስጥ ጉልህ ድርሻ እንዲያበረክቱ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው ብለዋል፡፡

በማሻሻያ አዋጁ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የሚሰጣቸውና ቁጥጥር የሚደረግባቸው የካፒታል እቃዎች፣ የፋይናንስ ኩባንያዎች፣ የጠለፋ መድን ሰጪ ኩባንያዎች እና በዲጅታል ዘዴዎች የመድን አገልግሎት መስጠት የሚሉ የትኩረት ነጥቦች መካተታቸውን ነው አንባሳደር መስፍን ያብራሩት፡፡

የኢ... ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 26 ቀን 2012 / ለሁለቱ የፌዴራል ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ የፌዴራል መንግስት 2012 / እቅድ የያዘ የመክፈቻ ንግግር ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ስለሆነም በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 12/1 እና 7 መሰረት የፕሬዚዳንቷ የመክፈቻ ንግግር እና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸውን አቋም የድጋፍ ሞሽኙ በሚጸድቅበት ወቅት እንደሚገለጽ ተነግሯዋል፡፡

በመጨረሻም የምክር ቤቱ 4 ዓመት የስራ ዘመን 3 አስቸኳይ ስብስባ ቃለጉባኤ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡