null University of Gonder built huge libratory center by 769 million birr to fulfill the country technology sector.

ጎንደር የኒቨርስቲ የአገሪቱን ፍላጎት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመደገፍ በ769 ሚሊዮን ብር ግዙፍ ቤተ-ሙከራ ማዕከል አስገነባ፡፡

የሰው ሃብትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመስክ ምልከታ አደረገ፡፡

ዶክተር ደሳለኝ መንገሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሲሆኑ እንደ እሳቸው ገለጻ ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ሰዓት በ6 ካምፓሶች ውስጥ ከ50 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምርት ዘርፎች እያስተማረ እንዲሁም ምቹ የመማር ማስተማር ሂደትን በመፍጠርና የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችል ስራዎችን በመስራት ላይ እንዳለ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ20 ዓመታት ውስጥ የአገሪቱን ፍላጎት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመደገፍ እና የምርምር ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል ለማስቻል በሁሉም የትምህርት መስኮች ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንዳለ እና ለአብነትም በ769 ሚሊዮን ብር በ88 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ቤተ-ሙከራ ማዕከል ከአገርም አልፎ ለሌሎች አፍሪካ አገሮችም ጭምር ተምሳሌት የሚሆን እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲው እየተስፋፉ ያሉት ግንባታዎች ተማሪዎች ዕውቀታቸውን በተግባር አዳብረው በክህሎት የላቁ እንዲሆኑ በማድረጉ የሚደገፍ ቢሆንም ግንባታው በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ ያለመጠናቀቅና የተጠናቀቁትም በግብዓት አቅርቦት እጥረት አገልግሎት እየሰጡ አለመሆናቸውን ተመልክቷል፡፡

የዩኒቨርስቲው አመራሮች በበኩላቸው ችግሮቹ  በኮንትራክተሮች አቅም ማነስ፣ በአማካሪዎች የሚፈጠር የዲዛይን በጊዜ አለማጠናቀቅ ክፍተትና በካፒታል በጀት በቂ አለመሆን እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታ ወቅት ያናገራቸው የተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ዩኒቨርስቲው የሰላም የመማር ማስተማር ሂደትን ለመፍጠር ሌት ተቀን እየሰራ ቢገኝም ከውስጥ ይልቅ ከውጭ በሚመጣ ተፅዕኖ የሚፈጠር አለመረጋጋት እንዳለና በአካባቢው አልፎ አልፎ የሚሰሙት የጦር መሳሪያ ድምጽ እንደሚረብሻቸውም ጠቁመዋል፡፡

ተማሪዎች ህብረትም በዩኒቨርስቲው የተማሪዎች አገልግሎት የተሻለ ለማድረግ በምግብ፣ በመዝናኛና በህክምና ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች ቢኖሩም ከዩኒቨርስቲው አቅም ጋር ሲነጻጸር ገና መሰራት እንዳለበት ያነሳሉ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ዩኒቨርሲቲውን ኢ-ዩኒቨርስቲ ለማድረግ በICT ዘርፍ ዘመናዊ ግብዓቶችን ተጠቅሞ በኢንተርኔት በመታገዝ የቤተ-መፅሐፍት አገልግሎት ከመስጠትም ባሻገር በግቢው ውስጥ የሚደረጉ የእለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ለመከታተል 170 ካሜራዎች ተተክለው የደህንነት ስራ ለማስጠበቅ እየተሰራ ያለውን በጠንካራ ጎን አንስቷል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ሌላኛው በመስክ ምልከታው በሆስፒታሉ ስር ጨረራ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ በዘመናዊ ግብዓቶች በመታገዝ ደረጃውን የጠበቀና ተጠቃሽ የሚባል በመሆኑ የሚበረታታ ነው ቢባልም ለማሽኖች እድሳት በርካታ ገንዘብ እያወጡ መሆናቸው ለአጠቃቀም ክፍተት እየፈጠረ መሆኑን የሆስፒታሉ አመራሮች ስጋታቸውን ጠቅሰዋል፡፡