null Canadian parliamentary delegates declare condolence to Ethiopian Airline Boeing 737.

የካናዳ ፓርላማ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ላይ በደረሰው የመከስከስ አደጋ ሀዘናቸውን  ገለጹ፡፡

የህዝብ  ተወካዮች  ምክር   ቤት  ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሽታዬ ምናለ የካናዳን   ፓርላማ   ልዑክ  በጽ/ቤታቸው  ተቀብለው  አነጋግረዋል፡፡

የልዑካን  ቡድኑ  መጋቢት 1/2011 ዓ.ም በተከሰከሰው የኢትዮጵያ ቦይንግ አውሮፕላን ማዘኑን ተናግሯል፡፡

የልዑካን ቡድኑ  የሁለቱን ሃገራት   የእርስ በርስ ፓርላሜንታዊ  ግንኙነት ለማጠናከርና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደመጣ  ተገልጿል፡፡

 የኢትዮጵያ  መንግስት  የፖለቲካ ስነ-ምህዳሩን  ለማስፋት በአጭር  ጊዜ  ውስጥ   ያከናዎናቸውን  ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር  ቡድኑ  አድንቋል፡፡

ወ/ሮ ሽታዬ  በበኩላቸው በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ላይ በደረሰው አደጋ ሃዘናቸውን ገልጸው፤  የተጀመረው ሃገራዊ ለውጥ ከዳር እንዲደርስ መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች  ጋር በመነጋገር እየሰራ  እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

ሃገራዊ ለውጡ ቀጣይነት እንዲኖረው መንግስት የተለያዩ  የህግ ማሻሻያዎችን ማድረጉ እንዲሁም  በህዝቡ የተነሱ የስነ-ምጣኔ፣የማህበራዊና  ፖለቲካዊ ጥያቄዎችን   እየፈታ እንደሚገኝ ወ/ሮ ሽታዬ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ጋር ያላትን  ሁለንተናዊ  ግንኙነት በማጠናከር   በመልካም ጉርብትና ላይ   እንደምትገኝም ወ/ሮ ሽታዬ ለልዑካን ቡድኑ አክለው ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ ከአስፈጻሚ አካሉ ጋር እንዴት ተቀናጅቶ እንደሚሰራ እንዲሁም ስለ ቁጥጥርና ክትትሉ ክንዋኔዎች ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ ተደርጎላቸል፡፡

የሁለቱን  ሃገራት  የፓርላማ  ግንኙነት  አጠናክሮ ለማስቀጠልም በንግድ፣ በሰላምና በድህነት ቅነሳ ላይ ያተኮር  ግንኙነት እንደሚኖር  የልዑካን ቡድኑ ገልጿል፡፡