null Ethiopian Business and Investment Seminar opens in Japan

በውይይቱም ግጭቱ በተነሳበት ወቅት መንግስት አፋጣኝ ርምጃ ከመውሰድ ለምን እንደተቆጠበ፣ የሱፐርቪዥኑ ሪፖርት መዘግየቱንና ግጭቱ የተከሰተባቸውን ሁሉንም ቦታዎች የዳሰሰ አለመሆኑ የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሰጡት ምላሽ ችግሩን ለመቅረፍ የተደረገው እንቅስቃሴ ከችግሩ ውስብስብነት አንጻር ሲታይ ውስንነት እንዳለበት ጠቁመው፤ ለግጭቱ መከሰት መንስኤው በየደረጃው የሚገኙ የአመራሮች የመወሰን አቅም ውስነነት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ 

የሱፐር ቪዥኑ አስተባባሪ አቶ ጫኔ ሽመካ በበኩላቸው ሪፖርቱ የዘገየበት በወቅቱ በነበሩ ተደራራቢ ችግሮች ምክንያት መሆኑን  እና የሱፐርቪዥኑን የዳሰሳ ሪፖርት በተመለከተም ግጭቱ የተነሳባቸው ቦታዎች ሰፊ ከመሆናቸው አንፃር ያልታዩ ቦታዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አያይዘው አንስተዋል፡፡

የሱፐር ቪዥኑ ቡድን የውሣኔ ሀሳብ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሰፊ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ በሦስት ድምፅ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡