ይሳተፉ

የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ

Tigist T, modified 4 Months ago.

የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ

Padawan Posts: 29 Join Date: 15/03/18 Recent Posts
የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ዋና ዓላማ አገልግሎት አሰጣጥን ቅልጣፋ፣ ተደራሽ፣ ግልጽና ውጤታማ ማድረግ ሲሆን የአፈፃፀም ስልቱ ህገ-መንግስቱን መሠረት ያደረገና ዘለቄታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ የመልካም አስተዳደር መርሆዎችና አሠራሮች በሁሉም ዘርፍ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገሪቱ ህገ-መንግስት ዕውቅና የሰጣቸውን መሰረታዊ የዜጎችን መብትና ነፃነት በማክበርና በማስከበር፣ የመንግስትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችሉ ዘመናዊ የህዝብ አስተዳደር ሥርዓት በሁሉም የአስተዳደር እርከን ማስፈን አለባቸው፡፡ በአገሪቱ ህገ-መንግስታዊ መርሆዎች እና ኢትዮጵያ ያፀደቀቻቸው አለምአቀፍ ስምምነቶች ላይ የተመሠረተና ለመልካም አስተዳደር ሥርዓት ግንባታ መሠረት የሆነ ዘመናዊ የህዝብ አስተዳደር ሥርዓትን መገንባት ከሚያስችሉ ጉዳዮች መካከል ዋንኛውና ግንባር ቀደሙ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባና ሥርዓት ነው፡፡

ይምረጡ