የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጸደቀ
------------------
(
ዜና ፓርላማ) ጥቅምት 5፣ 2019 ዓ.ም፤ አዲስ አበባ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡

መንግሥት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማግስት መስከረም 25 ቀን፣ 2019 ዓ.ም አዲስ የመንግሥት ምስረታ ማድረጉን ተከትሎ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመረጡ የምክር ቤት አባላትን በአዲስ በማደራጀት ውጤታማ ስራ ለመስራት ስራ መጀመሩ ይታወቃል ፡፡

በዚህ መሰረት የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባር እና ኃላፊነት በአዲስ አደራጅቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴዎች ተግባር እና ኃላፊነት በአዲስ በማደራጀት ስያሜያቸው የተቀየሩ ተቋማት ስላሉ እና የመደመር መንግስትን ዋና ስትራቴጂ እቅድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አህመድ ሽዴ ገልፀዋል፡፡

የምክር ቤት አባላቱ አንዳንድ የፌዴራል መንግስት ተቋማት እንደየስራ ባህሪያቸው በእያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ መካተት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

በዚህ መሰረት ምክር ቤቱ የሚከተሉት አስራ ሶስት ቋሚ ኮሚቴዎች አፅድቋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴዎቹ፡-

1.
የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
2.
የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
3.
የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
4.
የሰው ሃብት ልማት፣ ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
5.
የጤና፣ ማህበራዊ ልማት እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
6.
የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
7.
የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
8.
የኢንዱስቲሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
9.
የከተማ መሠረት ልማት እና ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
10.
የንግድ፣ ባህልና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
11.
የብሔራዊ ስትራቴጂ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣
12.
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና
13.
የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ናቸው፡፡

ለእያንዳንዱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምክትል ሰብሳቢ የሚኖሩት ሲሆን ሰብሳቢዎቹ በአፈጉ ባኤው አቅራቢነት በምክር ቤቱ ተመርጠዋል፡፡

ምክር ቤቱ ቋሚ የኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበ የውሳኔ ሃሳብ 03 /2019 አድርጎ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

(
በዓለማየሁ ጌቴ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/@FDREHOPR
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et
ይከታተሉ።