የገቢ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
null የገቢ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
Portal Admin
Modified 3 Years ago.
የገቢ ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚከተሉት ጉዳዮች ክትትልና ቁጥጥር ያከናውናል፡-
- የአገሪቱን የገንዘብእና የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ተግባራት በአግባቡ እየተከናወኑ መሆናቸውን፤
- የፌደራል መንግስት ታክስና ቀረጥ አስተዳደር እንዲሁም የመንግስት ገቢ አሰባሰብ በአግባቡ እየተከናወነ መሆኑን፤
- የፌደራል መንግሥት ዓመታዊና ተጨማሪ በጀት በአግባቡ ተዘጋጅቶ መቅረቡን እና መጽደቁን፤
- ለክልሎች የሚሰጥ ድጎማ በቀመሩ መሠረት መጽደቁን፤
- የፌደራል መንግስት ፋይናንስ እናንብረት አስተዳደር በአግባቡ መከናወኑን እናውጤታማ መሆኑን፤
- የአገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት እና ፍትሃዊነት እንዲሁም የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፓሊሲዎች መመንጨታቸውን እና በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን፣ ኢኮኖሚው በተገቢው መንገድ እየተመራ መሆኑን፤
- የአገሪቱ የልማት እቅድ እና የልማት ፕሮጀክቶች የአዘገጃጀትና አፈፃፀም ስርዓት መዘርጋቱን እንዲሁም በወቅቱ በስራ ላይ መዋሉን፤
- የአገሪቱ የስነ-ህዝብ ፓሊሲ መዘጋጀቱን፣ የማክሮ - ኢኮኖሚና የፊስካል ፖሊሲዎች መመንጨታቸውን እና በትክክል በስራ ላይ መዋላቸውን፤
- ትክክለኛ የሆነ የመንግስት የበጀት፣ የሂሳብ አያያዝ፣ የክፍያና የውስጥ ኦዲት ስርዓት መዘርጋቱንና በአግባቡ እየተፈፀመ መሆኑን፤
- የኢኮኖሚ ትብብሮችና ትስስሮች ከመደረጋቸው በፊት በአገሪቱ የኢኮኖሚ አፈፃፀም ላይ የሚያስከትሉት ውጤት የሚፈተሽ እና የሚገመገም መሆኑን፤
- በመንግስት የኢኮኖሚና የፋይናንስ ፖሊሲ መሠረት የመንግስት የልማት ድርጅቶች በአገሪቱ የኢኮኖሚና ንግድ እንቅስቃሴ ገንቢ ሚና እያበረከቱ መሆኑን፤
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች የስራ እንቅስቃሴ ትርፋማነትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን የሚያረጋግጥ መሆኑን፤
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች በህግ የተሰጣቸውን ተግባር በአግባቡ እየተገበሩ መሆኑን፤
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ በሆነ መንገድ መመራታቸውንና በአግባቡ ወደ ግል ይዞታ የተዛወሩ መሆናቸውን፤
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች የሚሰጡት የህዝብ አገልግሎት በአግባቡ መከናወኑን እና የውስጥና የውጭ መልካም አስተዳደር ጉዳዮች በተመለከተ፤
- የመንግስት የልማት ድርጅቶች አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማትን ጨምሮ በልማት ለሚሳተፉ ሌሎች ተቋማት የሚያደርጉት ድጋፍ።
- የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማትን የሚመለከቱ ፖሊሲዎች፣ ህጎች፣ ስትራቴጂዎች እና እቅዶች በአግባቡ በሥራ ላይ መዋላቸውን፤
- የሚከታተላቸውና የሚቆጣጠራቸው ተቋማት የተመደበላቸውን በጀት በአግባቡና በውጤታማነት በስራ ላይ ማዋላቸውን፡፡
ተ.ቁ | የተጠሪ መስሪያቤቶች ስም ዝርዝር |
1 | የገንዘብ ሚኒስቴር |
2 | የገቢዎች ሚኒስቴር |
3 | ፕላን እና ልማት ኮሚሽን |
4 | የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ |
5 | የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት |
6 | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ |
7 | የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት |
8 | የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ |
9 | የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር |
10 | የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ |
11 | የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ |
12 | የጉምሩክ ኮሚሽን |