ኮከስ
የሴቶች ኮከስ
1/ የሴቶች እና ህፃናት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሴቶች ኮከስ የሚከተሉት ተግባራት
ይኖሩታል፦
ሀ) የሴት የምክር ቤት አባላት የልምድ ልውውጥ ያካሄዳል፤
ለ) የሴቶች መብትና ተጠቃሚነትን በሚመለከቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ምክክር ያካሄዳል፤
ሐ) የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ያከናውናል፤
መ) ከክልል ሴቶች ኮከሶች ጋር ግንኙነት ያደርጋል።
2/ የሴቶች ኮከስ ተጠሪነት ለአፈጉባዔው ይሆናል፣ የኮከሱ ዝርዝር አደረጃጀትና አሰራር በዚህ ደንብ መሰረት በሚወጣ
መመሪያ ይወሰናል።