ይሳተፉ

መንግሥት ሠራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

Portal Admin, modified 2 Years ago.

መንግሥት ሠራተኞች ጡረታ ለመደንገግ የወጣ አዋጅ

Youngling Posts: 4 Join Date: 22/01/18 Recent Posts
አቅም በፈቀደ መጠን መንግሥት ማህበራዊ ዋስትና ሽፋን በማስፋፋት ለዜጎች እንዲደርስ ለማድረግ እንደሚሠራ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 90(1) ተመልክቷል፡፡ የሕገ-መንግስቱ ድንጋጌ በመከተል ልዩ ልዩ የማህበራዊ መድህን(Social Insurance) አዋጆችንና የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ወጥቶ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ የማህበራዊ መድህን ሕጎች አንዱ የመንግሥት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 714/2003  ሲሆን አዋጁ ወጥቶ ሥራ ላይ ከዋለ 10 ዓመት ያህል ሆኗል፡፡ በዚህ ወቅት የዐቅዱን ሽፋን ለማስፋትና አንዳንድ ድንጋጌዎችን ግልጽ ለማድረግ በተወሰደ ደረጃ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡
መንግሥት የዜጎችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት ተጠቃሚነት ለማሳደግ በአገር አቀፍ ደረጃ ሪፎርም እያካሄደ ከመሆኑም በላይ በየዘርፉ በሚሰጡ አገልግሎቶች የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡በመንግስት አገልግሎት ጡረታ ዐቅድ (Pension Scheme) ለሚሸፈኑ ባለመብቶች ፈጣን፣ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታ ለማሳደግ እንዲሁም ግልጽ የፈንድ አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋት የጡረታ አዋጁን አንዳንድ ድንጋጌዎችን ማሻሻል አስፈላጊ ይሆናል። ከዚሁ አንጻር በጡረታ አዋጁና መመሪያዎች ማስፈጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የአስተዳደር ሥርዓቱን ግልጽ ለማድረግ በአንዳንድ የአዋጁ ድንጋጌዎች ላይ የተደረገው ማሻሻያ እና ምክንያቱ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ይምረጡ