(ዜና ፓርላማ) ታህሳስ 08፣ 2018 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ ስብሰባቸውን የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ናሬንድራ ሞዲ በተገኙበት አካሂደዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በጋራ ስብሰባው መክፈቻ ላይ እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ህንድ ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የትስስር ታሪክ እንዳላቸው አፈ ጉባኤው አስታውሰው፤ ግንኙነቱን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና ሕንድ መካከል ያለው ግንኙነት በታሪክ፣ በባህል፣ በትምህርት፣ በንግድ እና በተለያዩ ዘርፎች የተሳሰረ መሆኑንም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ እና ህንድ መንግስታት መካከል ያለው የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ሁለቱ ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትና አጋርነት ማደግ እንዳለበትም አፈ ጉባኤው አንስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝትም ይህንን የሚያጠናክር እንደሆነ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጠቅሰዋል።

(በ አበባው ዮሴፍ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ

https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም

https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር

http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት

www.hopr.gov.et ይከታተሉ።