ኢትዮጵያና ካዛኪስታን የፓርላማና የኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተወያዩ

--------------------

(ዜና ፓርላማ ) ጥቅምት 25 ቀን፣ 2019 ዓ.ም.፤

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አህመድ ሽዴ በኢትዮጵያ ከካዛኪስታን አምባሳደር ዣላጋስ አዲልባየቭ ጋር የሁለቱን አገሮች የፓርላማና የኢኮኖሚ ትብብር ስለማጠናከር ተወያዩ።

አፈ ጉባኤው ኢትዮጵያ ከካዛኪስታን ጋር በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎች መስኮች ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ገልፀዋል። ትብብሩን ለማጎልበት ሁለቱ አገሮች በቅርበት እንደሚሠሩም አስረድተዋል።

አምባሳደሩ የሁለቱ አገሮች ግንኙነት በተለያዩ መስኮች እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ በአገሮቹ መሪዎች በተደረሱ የትብብር ስምምነቶች ላይ በመመሥረት የልምድ ልውውጡን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

አምባሳደሩ አክለውም የሁለቱ አገሮች የንግድ ልውውጥ ባለፈው ዓመት ከ61 በመቶ በላይ ማደጉን ገልፀዋል።

የንግድ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማሳደግ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ማስፋትና ሁለቱ አገሮች ከእርስ በርስ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተሞክሮ መማማር እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

በውይይቱ የሁለትዮሽ የፓርላማ ቡድኖችን ማቋቋምና ማጠናከር፣ እንዲሁም የሁለቱ ፓርላማዎች ባለሙያዎች ልምድ እንዲለዋወጡ ማድረግ እንደሚገባ ተነስቷል።

​(በ አምላኩ ነጋ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ

https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም

https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር

http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት

www.hopr.gov.et ይከታተሉ።