‎የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ዜጎች የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

‎------------------------

‎(ዜና ፓርላማ) መጋቢት 25፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ሳቢያ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ10 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

‎‎የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶን ጨምሮ፣ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር፣ የምክር ቤት አባላትና የጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎች በዞኑ በአካል ተገኝተው የምክር ቤቱን አጋርነት አሳይተዋል።

‎‎የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ሎሚ በዶ፤ በዞኑ በተከሰተው አደጋ ምክንያት በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ጉዳት እጅግ ማዘናቸውን ገልፀው ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል።

‎‎ምክር ቤቱ ያለውን አጋርነት ለማሳየትም የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለጋሞ ዞን አስተዳደር ያስረከቡ ሲሆን ዜጎቸን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ተግባር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

‎‎የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) ምክር ቤቱ ላሳየው ፈጣን ምላሽና አጋርነት በዞኑ ሕዝብና በአስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

‎‎እንዲህ ያሉ ድጋፎች የተረጂዎችን ሞራል ከመገንባት ባለፈ፣ መልሶ የማቋቋም ሥራውን እንደሚያቀላጥፉ ጠቁመዋል።

‎‎(በ አገሪቱ ጌቴ)

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament

በዩቲዩብ

https://www.youtube.com/@FDREHOPR

በቴሌግራም

https://t.me/ParlamaNews

በትዊተር

http://twitter.com/fdrehopr

በዌብሳይት

www.hopr.gov.et ይከታተሉ።